የረመዳን ሁነቶች

ከረመዳን በፊት | قبل رمضان

ታዋቂ ኮርሶች

Islamic knowledge from the source!

ኢስላማዊ ዕውቀትን ከምንጩ !

የቁርዓን ተፍሲር በአማርኛ

0% Complete
0/12 Steps

የአረበኛ ቋንቋ ትምህርት

0% Complete
0/8 Steps
Enrolled

የሕይወት ክህሎት ስልጠና

0% Complete
0/0 Steps

እኛ ማን ነን?

ኢማሙ አል ቡኻሪ ኢስላሚክ ማኅበር (IBIA) ሥሩን ያገኘው በ21ኛው ክፍለ ዘመን በአሥረኛው መጨረሻ ላይ ሲሆን ሙስሊሙ ለመስገድ፣ ለመማር እና ለመተሳሰብ በአንድ ላይ በመጣበት ወቅት ነው። IBIA በ2015 በይፋ የተቋቋመ ሲሆን ከጅምሩ በአዲስ አበባ ትልቁ እና በአባልነት ላይ የተመሰረተ  ኢስላማዊ ድርጅት ለመሆን በቅቷል።

ራዕይ

ማዕከሉ በዲን ሥራ ላይ ባለው ተደራሽነትና የሥራ ጥራት፣ እንዲሁም ለኢስላማዊ አንድነት፣ ለሰላምና ለማህበራዊ ስኬት መረጋገጥ ሐይማኖቱን አውቆ የተገበረ፣ የሐይማኖቱን ክብር ለመጠበቅ ቀናኢ የሆነ፣ ኢስላማዊ እሴቶችን አዳብሮ ወደ ሌላ አካል ለማስተላለፍ ብቁ የሆነ ማህበረሰብ በመገንባት ሀገር አቀፍ እውቅና የተቸረው ማዕከል ሆኖ ማየት ነው።

ተልዕኮ

ከአጋሮቹ ጋር በመተባበር ኢስላማዊ እውቀትን በመማርና በማስተማር፣ ኢስላማዊ ስነ-ምግባርን በማላበስ የኢስላምን ትክክለኛ ገፅታ ማንጸባረቅ እና ለዚህ ዓላማ ስኬት አስፈላጊውን አስተዋጽኦ ማድረግ ነው።

ዋና ዓላማ

ኢስላማዊ እውቀትን በማስረጽ፣ ፍጡርን ከፈጣሪ ጋር በማስተዋወቅ ኢስላማዊ ዕውቀትን ወደ ተግባር የሚቀይር ትውልድ መፍጠር።